Pages

Tuesday, September 13, 2011

የዘመናት ጌታ (መዝሙር)- ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ



የዕለት የዓመት
የዕለት የዓመት የዘመናቱ ጌታ






ለዚህ ላደረስከኝ ዘመኔን ሳትገታ
አቀርብልሃለሁ የክብር ሰላምታ /፪/
      ኑ እናመስግን ከልባችን
     የሰማዩን አባታችንን
     ከዚህ ዕለት ከዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
የሰው ልጆች ዕድሜ ጥንቱንም ሲጀመር
ምን ቢወጣ ቢወርድ ቢበዛ ቢደመር
አንድ ቀን አይሞላም እንዳንተ አቆጣጠር /፪/
     አዝ…
ስለዚህ አምላክ ሆይ ክቡር ነው ቅዱስ ነው
ወዳንተ እንዲመለስ ቀን የሰጠኸው ሰው
ደካማ ነውና ሰው ዕድሜ ከራበው /፪/
     አዝ…
እጅግ አደንቃለሁ የአምላክን ጥበብ
ምድርን በአበባ ሰማዩን በኮከብ
እንዳሸበረቃት አስተውዬ ሳስብ /፪/
      አዝ…
በከንቱ ጊዜአችን ፈጽሞ እንዳይጠፋ
በርትተን ከሠራን ያላንዳች ነቀፋ
አምላክ የሚሰጠን አለን ፍጹም ተስፋ /፪/
አዝ…
ከንቱ ካሳለፍኩት ጊዜዬን በዋዛ
ምን ያደርግልኛል ዘመኔ ቢበዛ
ደግሞም በጠቅላላው ዓለምን ብገዛ /፪/
አዝ…
ወርሃ ክረምት አልፎ መስከረም ሲጠባ
ምድር በልምላሜ ስታጌጥ በአበባ
እናምናለን ላንተ ምስጋና እንዲገባ /፪/

E.O.T.C: Ethiopian Orthodox Tewahedo Church A.M.H.K.M.S.S: Ambo Meserete Hiwot Kidane Meheret Sunday School

1 comment:

  1. እግዚአብሔር ይስጥልኝ በጣም ብዙ ደክሜ ኘበር ይሄን መዝሙር ለማግኘት በጣም አመሰግናለሁ🙏👍💕

    ReplyDelete