Pages

Tuesday, November 2, 2010

ብክዩ ኅዙናን ሃልየክሙ ስደታ ለማርያም ፤ እናንተ ርኅሩኃን ሆይ የድንግል ማርያምን ስደት በማስታወስ አልቅሱ፡፡ እዘኑ፡፡

 ማኅሌተ ጽጌ
ማኅሌተ-ጽጌ የሚለው ቃል ከሁለት የግዕዝ ቃላት በመጣመር የተገኘ ሲሆን ትርጉሙን ለመረዳት ማኅሌትና ጽጌ የሚሉትን በተናጠል እንመልከት፡፡
ማኅሌት፡ - ምሥጋና፣ ወረብ፣ ለዘብ፣ መወድስ ማለት ነው፡፡ የመዘመር ሀብት የተሰጠው ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሐር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት በመንፈስ ወደ ሰማይ ተነጥቆ ልብሱን እስኪጥል ድረስ በስሜት ሳሆን በመንፈስ ዘምሯል አመስግኗል፡፡ 2ኛ ሳሙ 6፡12-8፡፡ በዚህ የትርጓሜ ጽሁፍም “እስከመነነቶ ሜልኮል ቅድመ ታቦተ ሕግ ከመዘፈነ” ብሎ ያመጣዋል፡፡ ወደፊት የምንመለከተው ይሆናል፡፡

የማኅሌት ትርጉም ምሥጋና መሆኑን ከገለጽን ጽጌ የሚለውን ትርጒም ደግሞ እናያለን፡፡

  
አበባ ድንግል ከፍሬ ክርስቶስ ጋር

ጽጌ፡- ትርጉሙ አበባ የፍሬ ምልክት ማለት ሲሆን ፤ ማኅሌተ ጽጌ ብሎ ሲናበብ በአበባና በፍሬ የተመሰሉት ድንግል ማርያምና የማኅጸኗ ፍሬ ክርስቶስ የሚመሰገኑበት የአበባ ምሥጋና ማለት ነው፡፡
ይህ ማኅሌተ ጽጌ በትርጉም እንዲቀርብ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያትም ትርጕሙ፣ ምሥጢሩ፣ እና ታሪኩ የሚታወቀው የማኅሌት ባለሙያና የግእዝ ቋንቋ አዋቂ በሆኑት ሊቃውንት ስለሆነ በነርሱ ብቻ ተወስኖ እንዳቀር ባማሰብ ነው፡፡ “ሱራፌል፣ ኪሩቤል ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እያሉ እግዚአብሔርን በማመስገን ቀንና ሌሊት አያርፉም ከአንደበታቸውም ምሥጋና አይቋረጥም” ብሎ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያስረዳን ራእ 4፡5-11 በዘመነ ጽጌ  በሌላም ክብረ በዓል (ንግሥ) ጊዜ እንደ ሊቃውንቱ ምእመናንና ምእመናትም በተለይ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና መዘምራን የማኅሌቱ አገልግሎት ተሣታፊ በመሆናቸው በዜማው ጣዕም ብቻ እየተገለገሉና እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም “በእውኑ የምታነበውን ቃል ትርጕመሙን፣ ምሥጢሬን ታውቀዋለህን?” ብሎ ሐዋርያው ፊልጶስ ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ እንደነገረው፤ ትርጕሙን ተረድተው የበለጠ እናት ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ ሃይማኖታቸውን ጠብቀው እንዲያስጠብቁ ነው፡፡ ከትርጉሙ፣ ከምሥጢሩ፣ ከሐተታው (ከገለጻው) ውጪ ደራሲው (አባ ጽጌ ድንግል) በዚህ ማኅሌተ ጽጌ ውስጥ ስም እየጠቀሰ እንዲሁም ስም ሳይጠቅስ በንባብ ምሥጢር ብቻ የተናገራቸው ሁሉ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ስማቸውና ታሪካቸው በግልጽ ተጽፎ ይገኛል፡፡ የማኅሌተ ጽጌ ደራሲ ኢትዮጵያዊው ሊቅ እመቤታችን ድንግል ማርያምንና ልጇን መድኃኔለምን በወይን  ሐረግ፣ በጽጌረዳ አበባ፣ ሌላም መመሰል በሚገባቸው በልዩልዩ ምሳሌዎች ሁሉ እየመሰለ የደረሰው ግሩም የጸሎት መጽሐፍ ነው፡፡ በመሆኑም ከ85 በላይ ታሪኮችን የያዘ ልዩ ጽሑፍ መሆኑን ከወዲሁ ለአንባብን በደስታ እየገለጽን  እግዚአብሔር በሊቃውንቱ ልቡና አድሮ የሚናገረው ምሥጢር እንደ ውቅያኖስ ቢቀዳ ቢቀዳ አያልቅምና አልፎ አልፎ የንባብ መለያየት ቢኖርም ማለት በበዓታ፣ በግምጃ ቤት፣ በተለያዩ ሊቃውንት ሁሉ የሚነገረው ንባብ በትርጕምና በምሥጢር እስካልተለያየ ድረስ አቀራረቡ (ዝግጅቱ) በቅንፍ ሆኖ ቀርቧል፡፡ ለምሳሉ፣ ዘኒ /ዘንተ/ ስብሐት ወዘኒ/ወዘንተ/ ማኅሌት እንደ ማለት ነው፡፡ to read and download "ማኅሌተ ጽጌ" Geez version press this link http://ethiopianorthodox.org/amharic/seasonal/zemenetsige/mahletetsiege.pdf

የማኅሌተ ጽጌ ደራሲ
ይቀጥላል….
የእመቤታችን አማላጅነትና ረድኤት የልጇ ቸርነት አይለየን፡፡ አሜን፡፡

Thursday, October 21, 2010

tewahedomedia.org

tewahedomedia.org

E.O.T.C: Ethiopian Orthodox Tewahedo Church A.M.H.K.M.S.S: Ambo Meserete Hiwot Kidane Meheret Sunday School

Wednesday, October 20, 2010

How do I add Reactions to my blog?

ውድ የ “ቤት ለእንግዳ” ብሎግ ጎብኚዎች ይህ ብሎግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ሥርዓትና ትውፊት ዙርያ የሚያጠነጥን ሲሆን የጅማሬና የፍጻሜ ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር በፈቀደ መጠን ከመጻሕፍት ያገኘኋቸውን፤ ከአባቶች የተማርኩትን እና ቢሻሻል የምለውን ሁሉ ለማቅረብ ጥረት አደርጋለሁ፡፡ የሁላችሁም ጸሎት እንዳይለየኝ እየተማጸንኩ እንኳን በደህና መጣችሁ እላለሁ፡፡

የልዑል እግዜአብሔር ቸርነት የቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕተ ንጹሐን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ንጽህት የሆነችው የአባቶቻችን የቅዱሳን ጸሎት ዘወትር አይለየን፡፡ አሜን፡፡


E.O.T.C: Ethiopian Orthodox Tewahedo Church A.M.H.K.M.S.S: Ambo Meserete Hiwot Kidane Meheret Sunday School

Tuesday, October 19, 2010

ጽጌ

የእመቤታችን ስደት ከማኅሌተ ጽጌ

By Tade Tekle · Wednesday, October 19, 2010
ጽጌ የሚለው ቃል የግዕዝ ሲሆን አበባ የሚል የአማርኛ ፍቺ ይሰጠናል፡፡ ከመስከረም ፳6 እስከ ሕዳር 6 ድረስ ያለው ወቅት “ወርሃ ጽጌ” የሚባል ሲሆን ስያሜው በሀገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ተፈጥሯዊ ሁኔታ ያገናዘበ ነው፡፡ በዚህ ወቅት የክረምቱ ጨለማ ተገፎ ብርሃን የሚፈነጥቅበት፤ አበቦች ለዓይን ማራኪ የሆነውን ሰሎሞን እንኳን በክብሩና በጥበቡ ሊለብሰው ያልተቻለውን በእደ ሰብእ ያልተዘጋጀውን ውብ የሆነ ልብሳቸውን ተጎናጽፈው የሚመለከታቸውን ሁሉ ትኩረት የሚስቡበት፤ ለአፍንጫ ተስማሚ የሆነውን ጥዑም መዓዛቸውንም እንካችሁ ብለው ያለስስት የሚቸሩበት፤ አእዋፍ ዝማሬያቸውን ከወትሮው በላቀ ሁናቴ ለጆሮአትን የሚያንቆረቁሩበት ንቦች ከአበባ አበባ እየዘለሉ ጣፋጭ ማርን የሚያዘጋጁበት ሁሉ አምሮ ሁሉ ደምቆ አዲስ ሆኖ የሚገኝበት ወቅት በመሆኑ፤ ይህን ጊዜ ወርሃ ጽጌ፣ ዘመነ ጽጌ፣ ተብሎ መሰየሙን ልብ ይሏል፡፡

“አበቦችን እንዴት እንዲያድጉ ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዲቱ አለበሰም።ሉቃ 12፥27
በዚህ ወቅት ባሉት አርባ ዕለታት በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን አንድ ትልቅ ጉዳም ይታሰባል፡፡ የእመቤታችን ስደት፡፡
“እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ። ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።” እንዲል  ማቴ 213

በዚህ ወቅት የኢትዮጵያዊው ሊቅ የአባ ጽጌድንግል ውብ ድርሰት የሆኑት “ማኅሌተ ጽጌ” እና “ሰቆቃወ ድንግል” የተሰኙት የእመቤታችንን የስደት ጉዞ የሚያስቃኙ ዝማሬዎች በሊቃውንት አባቶች፣ በአባቶች እናቶችና ወጣቶች ሲዘመትር ይታራል፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች ከእመቤታችን ስደት በረከትን ያገኙ ዘንድ “ጾመ ጽጌ፣ የጽጌ ጾምን” በፈቃዳቸው የጾሙታል፡፡

እኛም ከሃገር ለሃገር ያለ ረዳት ዘመድ አንድ ልጇን መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ የተንከራተተችውን እመቤት እናስብ ዘንድ አበው በማኅሌት ሲዘምሩ ከሚያደርሱት አርኬ፣ ከሚወርቡት ወረብና ከሚመረግዱት ዚቅ በጥቂቱ በተከታታይ ለማስቃኘት እንሞክራለን፡፡ ለዛሬው እነሆ፡፡
በመጀመሪያው እሁድ የሚጸነጸል አርኬ
ጽጌ አስተርአየ ሠሪጾ እምአፅሙ፡፡
ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ፡፡
ወበእንተዝ ማርያም ሶበ ሐወዘኒ መዐዛ ጣዕሙ፡፡
ለተአምርኪ አኃሊ እሙ፡፡
ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ

በመጀመሪያው እሁድ የመጀመሪያው ዓቢይ ወረብ
ጽጌ አስተርአየ ሠሪጾ እም አፅሙ ለዘአምኃኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ (በይነ) ሰላሙ (2)
ወበእንተዝ ማርያም ሶበ ሐወዘኒ መዐዛ ጣዕሙ(2)
ከማኅሌቱ በረከት ያገኙ ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው፡፡
ከእመቤታችን በረከት ይክፈለን የምግባረ ሰናይ የተሰደድነውንም ወደ ሰማያዊት ሃገር ወደ ሆነም በጎ ምግባር ይመልሰን አሜን፡፡


Wellcome



ውድ የ “ቤት ለእንግዳ” ብሎግ ጎብኚዎች ይህ ብሎግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ሥርዓትና ትውፊት ዙርያ የሚያጠነጥን ሲሆን የጅማሬና የፍጻሜ ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር በፈቀደ መጠን ከመጻሕፍት ያገኘኋቸውን፤ ከአባቶች የተማርኩትን እና ቢሻሻል የምለውን ሁሉ ለማቅረብ ጥረት አደርጋለሁ፡፡ የሁላችሁም ጸሎት እንዳይለየኝ እየተማጸንኩ እንኳን በደህና መጣችሁ እላለሁ፡፡
የልዑል እግዜአብሔር ቸርነት የቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕተ ንጹሐን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ንጽህት የሆነችው የአባቶቻችን የቅዱሳን ጸሎት ዘወትር አይለየን፡፡ አሜን፡፡

ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ