ብክዩ ኅዙናን ሃልየክሙ ስደታ ለማርያም ፤ እናንተ ርኅሩኃን ሆይ የድንግል ማርያምን ስደት በማስታወስ አልቅሱ፡፡ እዘኑ፡፡
ማኅሌተ-ጽጌ የሚለው ቃል ከሁለት የግዕዝ ቃላት በመጣመር የተገኘ ሲሆን ትርጉሙን ለመረዳት ማኅሌትና ጽጌ የሚሉትን በተናጠል እንመልከት፡፡
ማኅሌት፡ - ምሥጋና፣ ወረብ፣ ለዘብ፣ መወድስ ማለት ነው፡፡ የመዘመር ሀብት የተሰጠው ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሐር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት በመንፈስ ወደ ሰማይ ተነጥቆ ልብሱን እስኪጥል ድረስ በስሜት ሳሆን በመንፈስ ዘምሯል አመስግኗል፡፡ 2ኛ ሳሙ 6፡12-8፡፡ በዚህ የትርጓሜ ጽሁፍም “እስከመነነቶ ሜልኮል ቅድመ ታቦተ ሕግ ከመዘፈነ” ብሎ ያመጣዋል፡፡ ወደፊት የምንመለከተው ይሆናል፡፡
የማኅሌት ትርጉም ምሥጋና መሆኑን ከገለጽን ጽጌ የሚለውን ትርጒም ደግሞ እናያለን፡፡
አበባ ድንግል ከፍሬ ክርስቶስ ጋር
ጽጌ፡- ትርጉሙ አበባ የፍሬ ምልክት ማለት ሲሆን ፤ ማኅሌተ ጽጌ ብሎ ሲናበብ በአበባና በፍሬ የተመሰሉት ድንግል ማርያምና የማኅጸኗ ፍሬ ክርስቶስ የሚመሰገኑበት የአበባ ምሥጋና ማለት ነው፡፡
ይህ ማኅሌተ ጽጌ በትርጉም እንዲቀርብ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያትም ትርጕሙ፣ ምሥጢሩ፣ እና ታሪኩ የሚታወቀው የማኅሌት ባለሙያና የግእዝ ቋንቋ አዋቂ በሆኑት ሊቃውንት ስለሆነ በነርሱ ብቻ ተወስኖ እንዳቀር ባማሰብ ነው፡፡ “ሱራፌል፣ ኪሩቤል ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እያሉ እግዚአብሔርን በማመስገን ቀንና ሌሊት አያርፉም ከአንደበታቸውም ምሥጋና አይቋረጥም” ብሎ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያስረዳን ራእ 4፡5-11 በዘመነ ጽጌ በሌላም ክብረ በዓል (ንግሥ) ጊዜ እንደ ሊቃውንቱ ምእመናንና ምእመናትም በተለይ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና መዘምራን የማኅሌቱ አገልግሎት ተሣታፊ በመሆናቸው በዜማው ጣዕም ብቻ እየተገለገሉና እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም “በእውኑ የምታነበውን ቃል ትርጕመሙን፣ ምሥጢሬን ታውቀዋለህን?” ብሎ ሐዋርያው ፊልጶስ ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ እንደነገረው፤ ትርጕሙን ተረድተው የበለጠ እናት ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ ሃይማኖታቸውን ጠብቀው እንዲያስጠብቁ ነው፡፡ ከትርጉሙ፣ ከምሥጢሩ፣ ከሐተታው (ከገለጻው) ውጪ ደራሲው (አባ ጽጌ ድንግል) በዚህ ማኅሌተ ጽጌ ውስጥ ስም እየጠቀሰ እንዲሁም ስም ሳይጠቅስ በንባብ ምሥጢር ብቻ የተናገራቸው ሁሉ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ስማቸውና ታሪካቸው በግልጽ ተጽፎ ይገኛል፡፡ የማኅሌተ ጽጌ ደራሲ ኢትዮጵያዊው ሊቅ እመቤታችን ድንግል ማርያምንና ልጇን መድኃኔ㗹ለምን በወይን ሐረግ፣ በጽጌረዳ አበባ፣ ሌላም መመሰል በሚገባቸው በልዩልዩ ምሳሌዎች ሁሉ እየመሰለ የደረሰው ግሩም የጸሎት መጽሐፍ ነው፡፡ በመሆኑም ከ85 በላይ ታሪኮችን የያዘ ልዩ ጽሑፍ መሆኑን ከወዲሁ ለአንባብን በደስታ እየገለጽን እግዚአብሔር በሊቃውንቱ ልቡና አድሮ የሚናገረው ምሥጢር እንደ ውቅያኖስ ቢቀዳ ቢቀዳ አያልቅምና አልፎ አልፎ የንባብ መለያየት ቢኖርም ማለት በበዓታ፣ በግምጃ ቤት፣ በተለያዩ ሊቃውንት ሁሉ የሚነገረው ንባብ በትርጕምና በምሥጢር እስካልተለያየ ድረስ አቀራረቡ (ዝግጅቱ) በቅንፍ ሆኖ ቀርቧል፡፡ ለምሳሉ፣ ዘኒ /ዘንተ/ ስብሐት ወዘኒ/ወዘንተ/ ማኅሌት እንደ ማለት ነው፡፡ to read and download " ማኅሌተ ጽጌ" Geez version press this link http://ethiopianorthodox.org/amharic/seasonal/zemenetsige/mahletetsiege.pdf
የማኅሌተ ጽጌ ደራሲ
ይቀጥላል….
የእመቤታችን አማላጅነትና ረድኤት የልጇ ቸርነት አይለየን፡፡ አሜን፡፡
No comments:
Post a Comment