Pages

Friday, September 30, 2011

የተሐድሶ መናፍቃን ቅሰጣ በሰሜን ከኢትዮጵያ እስከ ሰሜን አሜሪካ

part 1
የተሐድሶ መናፍቅ
ቤተ ክርስቲያንን ሊረከብ ሚናፍቅ
አላወቀም በቅዱሳን እንደምትጠበቅ
አዬ .... መስሎት
ተኩላው በእምዬ ላይ ቢያደባባት
ማስጠንቀቂያ ደወል ሆናት
የምትነቃበት ከመዘናጋት።
ማናልባት ምናልባት
በጐቿን ቢወስድም በማድባት
የሚሄዱት በጐች አይደሉም
በጐች ቢሄዱም በዚያው አይቀሩም
ካባው ሲገፈፍ የማንነቱ


በገሃድ ሲታወቅ ተኩላነቱ
በጐቹም ይመለሳሉ ወደ በረቱ።
አብ የተከለው አይነቀል
ወይን ኩርንችትን እንዳያበቅል
መራር አይሆን የበለስ ተክል
እንደዚሁ ሁሉ ምን ቢወስዱት በማባበል
የተዋሕዶ ልጅ ወደ እናቱ ይመለሳል።
ተው ተሐድሶ አትጃጃል
እዛው እንደለመድከው ከጉረኖህ ብትገባው ይበጅሃል
ተዋሕዶ ነቅቶብሃል።
ከነቁ አይገደዱ እንዲሉ ጃል።
part 2
part3



part 4

part 5



part 6


part 7


part 8




part 9




part 10




part 11




part 12


part 13




part 14




part 15










Tuesday, September 13, 2011

የዘመናት ጌታ (መዝሙር)- ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ



የዕለት የዓመት
የዕለት የዓመት የዘመናቱ ጌታ






ለዚህ ላደረስከኝ ዘመኔን ሳትገታ
አቀርብልሃለሁ የክብር ሰላምታ /፪/
      ኑ እናመስግን ከልባችን
     የሰማዩን አባታችንን
     ከዚህ ዕለት ከዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
የሰው ልጆች ዕድሜ ጥንቱንም ሲጀመር
ምን ቢወጣ ቢወርድ ቢበዛ ቢደመር
አንድ ቀን አይሞላም እንዳንተ አቆጣጠር /፪/
     አዝ…
ስለዚህ አምላክ ሆይ ክቡር ነው ቅዱስ ነው
ወዳንተ እንዲመለስ ቀን የሰጠኸው ሰው
ደካማ ነውና ሰው ዕድሜ ከራበው /፪/
     አዝ…
እጅግ አደንቃለሁ የአምላክን ጥበብ
ምድርን በአበባ ሰማዩን በኮከብ
እንዳሸበረቃት አስተውዬ ሳስብ /፪/
      አዝ…
በከንቱ ጊዜአችን ፈጽሞ እንዳይጠፋ
በርትተን ከሠራን ያላንዳች ነቀፋ
አምላክ የሚሰጠን አለን ፍጹም ተስፋ /፪/
አዝ…
ከንቱ ካሳለፍኩት ጊዜዬን በዋዛ
ምን ያደርግልኛል ዘመኔ ቢበዛ
ደግሞም በጠቅላላው ዓለምን ብገዛ /፪/
አዝ…
ወርሃ ክረምት አልፎ መስከረም ሲጠባ
ምድር በልምላሜ ስታጌጥ በአበባ
እናምናለን ላንተ ምስጋና እንዲገባ /፪/

E.O.T.C: Ethiopian Orthodox Tewahedo Church A.M.H.K.M.S.S: Ambo Meserete Hiwot Kidane Meheret Sunday School